በዞኑ ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሃብቶች በተለየ መልኩ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው የጉራጌ ዞን አስተዳደር ገለፀ!

ጳጉሜ 01/2017 (ወልቂጤ)

ወፈንቻ ሪል እስቴት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በወልቂጤ የሚያስገነባው የመኖሪያ መንደር የከተማውን ገጽታ የሚቀይር ግዙፍ ፕሮጀክት እንደሆነም ተገልፅጿል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ በዞኑ ፍቃድ ከተሰጣቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ወፈንቻ ሪል እስቴት መሆኑን እና ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገውን 5 ሄክታር መሬት ማመቻቸት መቻሉ በመግለፅ።

ፕሮጀክቱም በውስጡ የጉራጌን ባህልና እሴት የሚያሳዩ የመኖሪያ ቤቶች፣ የባንክ አገልግሎት፣ የነዳጅ ማደያ፣ የሬስቶራንት፣ የካፌ፣ የትምህርትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አገልግሎት የሚሰጡ ስፍራዎች የያዘ የዘመናዊ መንደር ተምሳሌት እንደሚሆን አስገንዝበዋል።

ፕሮጀክቱ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባ መሆኑን የገለፁት ክቡር አስተዳዳሪው ግንባታው ከአንድ ዓመት ተኩል ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃም አስረድተዋል።

የፕሮጀክቱ ባለቤቶች በሌሎች አካባቢዎች ያላቸው ልምድና አቅም በመጠቀም በፍጥነት ወደ ተግባር እንደሚገቡና ለአካባቢው ወጣትና ማህበረሰብ እድል እዲሆኑም አሳስበዋል።

በዞኑ ኢንቨት ለሚያደርጉ ባለሃብቶች ልዩ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው የገለፁት ክቡር አስተዳዳሪው፣ከዚህ ቀደም ኢቨስት ለማድረግ ቦታ ተረክበው ወደ ስራ ያልገቡ ባለሃብቶችም በአስቸኳይ ወደ ተግባር እንዲገቡም አሳስበዋል!!

የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በበኩላቸው፣ ከተማዋ ለኢንቨስትመንት ምቹና ተመራጭ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ ውጤት ማስገኘታቸውን በመግለፅ።

ከተማዋ ጽዱ፣ ውብና ማራኪ እንዲሁም ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ ግብ ተጥሎ እየተሰራ እንደሆነና በሶስቱም ክፍለ ከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ስራዎች ለከተማው እድገት አዲስ ምዕራፍ የከፈቱ መሆናቸው አውስተዋል።

ከተማዋ በእድሜዋ ልክ አለማደጓ በህብረተሰቡ ዘንድ ቁጭት ይፈጥር እንደነበር የገለፁት ከንቲባው፣ መንግስት ለኢንቨስትመንት የፈጠረው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው አስገንዝበዋል።

በከተማው መዋዕለ-ንዋያቸውን የሚያፈሱ ባለሀብቶች ለማነቃቃት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ከንቲባው፣ ወፈንቻ ሪል ስቴት አንዱ ማሳያ ስለመሆኑ በአብነት ጠቅሰዋል።

አቶ ሙራድ በመልዕክታቸው በጉብሬ ክፍለ ከተማ ዛሬ መሰረት ድንጋይ የተጣለለት ፕሮጀክት ለከተማው እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥበቃ ማድረግ እንደሚጠበቅበትም አሳስበዋል።

የወፈንቻ ሪል እስቴት ፕሮጀክት ማናጀር ኢንጂነር ታደለ በመልዕክታቸው በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክፍለ ከተማ ላይ የሚገነባው ወፈንቻ ሪል እስቴት በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ግንባታው በማጠናቀቅ ለምርቃት እንደሚበቃ በማስገንዘብ።
‎
‎ፕሮጀክቱ ከግንባታው ጀምሮ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ከመሆኑ ባሻገር የከተማው ገጽታ ለመቀየር ሚናው የጎላ መሆኑ ገልፀዋል።

Comments are closed.