የወልቂጤ ጤና ጣቢያ ከሀገር አልፎ በአፍሪካ ምርጥ ጤና ጣቢያ እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ሲሉ ዶ/ር አብድልቋድር ገልገሎ ገለጹ

ጥቅምት 27/2019(ወልቂጤ)

የኢትዮጵያ መድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ባለስልጣን ዋና ኃላፊ ክቡር ዶ/ር አብድልቋድር ገልገሎ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በመገኘት የወልቂጤ ጤና ጣቢያን ጉብኝት አድርገዋል።

ክቡር ዶ/ር አብድልቋድር ገልገሎ እንደገለፁት የወልቂጤ ጤና ጣቢያ በሀገር ደረጃ የማይበገረው የጤና ስርአት ለመገንባት የሚደረገው ጥረት ያቀላጠፈ እንደ ሀገር ሞዴልና ምሳሌ የሚሆን ተቋም ነው፦

ወልቂጤ ጤና ጣቢያ አዳዲስ ስራዎች በመስራት፣በየአመቱ ተጨማሪ ለውጥ በማሳየት እና ለችግሮች መፍትሄ በመስጠት ለህብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት አድንቀዋል።

የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ለማቀላጠፍ የዲጂታል አገልግሎት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት።

በመሆኑም በሀገር ደረጃ ከተመረጡ 17 ምርጥ የጤና ጣቢያዎች ግንባር ቀደም ሲሆን በቀጣይ ጤና ጣበያው በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ዶክተሩ በተቋሙ ችግር የሆነው የx ray ማሽን እንዲገባ በማስተባበር እንዲሁም ተጨማሪ የህክምና ቁሳቁሶች ደግሞ በስጦታ እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ወ/ማርያም እንደገለጹት የጤና ዘርፉ ግቦች ለማሳካት በተደረገው የጋራ ርብርብ የሕክምና ቁሳቁሶችን በማሟላት የሆስፒታሎችን አገልግሎት ማሻሻልና የተገልጋዮችን እንግልት መቀነስ ተችሏል።

በመሆኑም በዞኑ ስምንት ሁሉን አቀፍ የጤና ኬላዎች ግንባታ ተጀምሮ አራቱ ተጠናቀው አገልግሎት ሲሰጡ፣ ሰባት መሠረታዊ የጤና ኬላዎችም በአዲስ ስታንዳርድ ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጋቸውን አቶ መብራቴ ገልጸዋል።

በዞኑ ሶስት ተቋማት ከወረቀት ነፃ የዲጂታል አገልግሎት መስጠት እንደቻሉና የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን በሁሉም መዋቅሮች በመተግበር የአካባቢ ንጽህናንና ውበትን ማሻሻል መቻሉንም ጠቁመዋል።

ከዚህ ባለፈ የደም ልገሳ፣ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ፣ የወባና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች መከላከል እንዲሁም የማህበረሰብ ፋርማሲዎችን ማቋቋም ላይ ሰፊ ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል።

የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች በፍጹም ቁርጠኝነት መተግበር በመቻሉ የግለሰብን እና የጎዳና መጸዳጃ ቤቶች ደረጃና አጠቃቀም መሻሻላቸው ተናግረዋል።

ቀበሌዎችን ጽዱና ማራኪ በማድረግ እንዲሁም የገጠር ኮሪደር መነሻ የሆነው የጉራጌ <<የጀፎረ›› ውበት ጋር በማስተሳሰር እንደ ሃገር ተሞክሮ የሚወሰድበት ቦታ ማድረግ ተችሏል ሲሉ አቶ መብራቴ አስታውቋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለጹት የዘንድሮው 28ኛው ሀገር አቀፍ የጤና ጉባኤ መሪ ቃል የጤና ሥርዓቱን በራስ አቅም፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ በማጠናከር ለሁሉም ዜጎች ጥራት ያለውና ተደራሽ አገልግሎት ለማረጋገጥ ያለመ ነው።

ወልቂጤ ጤና ጣቢያም ከመደበኛ የጤና አገልግሎት ባሻገር የእናቶችና ሕፃናት ጤና፣ የድንገተኛ ሕክምና፣ የላቦራቶሪ፣ የፋርማሲ፣ የዓይንና የጥርስ ሕክምና እንዲሁም ሌሎች የጤና አገልግሎቶችን በተቀናጀ መልኩ እየሰጠ መሆኑን ከንቲባው ገልጸዋል።

በተለያዩ የጤና ፕሮግራሞችም እውቅና በማግኘት የተሞክሮ ልውውጥና የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ማዕከል መሆን ችሏል።

ከንቲባው አክለውም የመስክ ጉብኝቱ የጤና ተቋማት የለውጥ ጉዞና የተሻሻሉ አሠራሮችን ለመጋራት፣ ልምድ ለመለዋወጥና ያሉ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ጠቃሚ ዕድል ይፈጥራል።

የወልቂጤ ጤና ጣቢያ ስራ አስከያጅ አቶ በድሉ ሳህሉ በበኩላቸው ተቋሙ የዲጂታል ጤና ሥርዓትን በመተግበር ከወረቀት ነፃ አሠራርን እያስፋፋ፣ የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦትን እያጠናከረና የአገልግሎት ጥራትን እያሻሻለ ያለ ተቋም ነው ብለዋል።

በውይይቱ ከፌደራልና ከተለያዩ ክልሎች የተገኙ የተገኙ ሲሆን የወልቂጤ ጤና ጣበያ እያደረገው ያለው የጤና አገልግሎት አሰጣጥ እጅግ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ተቋሙ በየጊዜው አዳዲስ የጤና አገልግሎት ስራዎች በመስራት ለአብነትም በማህጸን በር ጫፍ ፣በወባ፣በእናቶችና ህጻናት፣ በድንገተኛ ፣በአይን ህክምና በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ላይ የተሰሩ ስራዎችና አድናቆታቸው ችረዋል።

ለዚህም መንግስት፣ የጤና ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *